የሀገር ውስጥ ዜና

ከጂቡቲ ወደብ ማዳበሪያና ስንዴ ወደ ሀገር ውስጥ ለማጓጓዝ ከጭነት ትራንስፖርት ማህበራት ጋር መግባባት ላይ ተደረሰ

By Meseret Awoke

April 20, 2022

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከጂቡቲ ወደብ ማዳበሪያና ስንዴ ወደ ሀገር ውስጥ ለማጓጓዝ ከጭነት ትራንስፖርት ማህበራት ጋር የጋራ መግባባት ላይ መደረሱ ተተገለጸ፡፡

ከጂቡቲ ወደብ ማዳበሪያና ስንዴ ወደ ሀገር ውስጥ ለማጓጓዝ ከጭነት ትራንስፖርት ማህበራት ጋር ዛሬ ምክክር ተድርጓል፡፡

የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒሰቴር ከ72 የጭነት ትራንስፖርት ማህበራት በኩል 1 ነጥብ 28 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያና ስንዴ ወደ ሀገር ውሰጥ በወቅቱ እንዲገባ ለማስቻል እና ለማህበራት በተሰጠው ኮታ ድልድል ላይ ነው የጋራ ውይይት ያደረገው፡፡

ማዳበሪያና ስንዴ ወደ ሀገር ውስጥ ማጓጓዝ ሀገራዊ ግዴታችን ነው ያሉት የማህበራት ተወካዮች÷ የማህበራት ተሽከርካሪዎች ላይ የሚደረገው ክትትልና ቁጥጥር ዝቅተኛ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የኮታ አመዳደብ መነሻ ሁኔታን እና የተመደበ የታሪፍ ክፍያን በሚመለከት የጸጥታ ሁኔታን፣ የመጋዘን፣ ከጫኝና አውራጃ ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮቸን እንዲሁም በጂቡቲ መሰመር በኩል ያለው የመንገድ መበላሽት ላይ ውይይት መደረጉ ተገልጿል፡፡

በውይይት መድኩ የኢትዮጵያ ማሪታይም ጉዳዮች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር የኋላሽት ጀመረ እና የመንገድ ፈንድና ደህንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር አቶ አብዱልበር ሸምሱ መገኘታቸውን ከትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላታል፡፡

ከጂቡቲ ወደብ ማዳበሪያና ስንዴ ወደ ሀገር ውስጥ ለማጓጓዝ ከጭነት ትራንስፖርት ማህበራት ጋር የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷልም ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!