Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ማሪፖል ከተማን መቆጣጠሯን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ ከአዞቭስትታል ብረት ፋብሪካ ውጭ ማሪፖል ከተማን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሯን አስታውቃለች፡፡
የመከላከያ ሚኒስትሩ ሰርጌይ ሾይጉ እንደገለፁት የሩሲያ ጦር የወደብ ከተማ የሆነችውን ማሪፖልን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን ለፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን አሳውቀዋል፡፡

ይሁን እንጂ ከ2 ሺህ የሚበልጡ የዩክሬን ወታደሮች አሁንም በከተማዋ አቅራቢያ በሚገኘው አዞቭስትታል ብረት ፋብሪካ ውስጥ መሽገው እየተዋጉ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
ሩሲያ መጋቢት ወር ለመጀመሪያ ጊዜ ማሪፖልን ስትከብ 8 ሺህ 100 የዩክሬን ወታደሮች፣ የውጭ ቅጥረኛ ወታደሮች እና ብሄራዊ ታጣቂዎች በከተማዋ መሽገው እንደነበር አብራርተዋል፡፡
ሚኒስትሩ በተጨማሪም የዶንባስ ሪፐብሊካኖች በማሪፖል አቅራቢያ የሚገኘውን የአዞቭስታል ፋብሪካ ለመያዝ ከሶስት እስከ አራት ቀን ሊፈጅባቸው እንደሚችል አመላክተዋል፡፡
በከተማዋ ከ1 ሺህ 400 በላይ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን የፈቱ ሲሆን 142 ሺህ ዜጎች ደግሞ የሩሲያ ጦር ከበባን ተከትሎ ከተማዋን ለቀው መውጣታቸውን አር ቲ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.