Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ 10 ሺህ ተገጣጣሚ ቤቶች በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ ለነዋሪዎች ለማስተላለፍ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ 10 ሺህ ተገጣጣሚ ቤቶችን ግንባታ በሁለት ዙር በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ ለነዋሪዎች ለማስተላለፍ እየተሰራ መሆኑን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በአዲስ አበባ የነዋሪው ሕዝብ ቁጥር እያሻቀበ በመምጣቱ የመኖሪያ ቤት እጥረት በስፋት እየተስተዋለ ስለሆነ ይህን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለማቃለል በመንግስት በኩል የተለያዩ የመፍትሄ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው ተብሏል፡፡

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዲኤታ ሄኖስ ወርቁ÷ የመኖሪያ ቤት ፈላጊዎች ቁጥር እጥረቱን ለማቃለል የተገጣጣሚ ቤቶች ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

ከዚህ በፊት በ40/60፣ 20/80 እና 10/90 የቤት ልማት ልማት ፕሮጀክት ሲከናወን መቆየቱን ጠቅሰው÷ ከቤት ከፈላጊው ብዛት አንፃር የፕሮጀክቶች ክንውን በሚፈለገው ልክ አለመሆኑን ገልጸዋል።

በዚህ ዓመትም በግንባታ ሂደት ላይ የነበሩ 68 ሺህ ቤቶች ግንባታቸው ተጠናቆ ለተጠቃሚ ቢተላለፉም÷ ቀሪ 4 ሺህ ቤቶች በግንባታ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በመጀመሪያው ዙር 5 ሺህ ቤቶችን በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ለተጠቃሚው ለማስተላለፍ ግንባታው እየተከናወነ መሆኑን ነው የገለጹት።

የመኖሪያ ቤት እጥረት ችግር በመንግስት ጥረት ብቻ የሚፈታ ባለመሆኑ ሌሎች አማራጮች አንዲኖሩ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የውጭ ባለሃብቶች በዘርፉ እንዲሰማሩ ማድረግን ጨምሮ የግል አልሚ ባለሃብቱን ከማህበራት ጋር በማቆራኘት ለቤት ፍላጊዎች ምላሽ ለመስጠት በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አመላክተዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.