Fana: At a Speed of Life!

በአሸባሪው ህወሓት ጉዳት ከደረሰባቸው 42 ሆስፒታሎች 36 ያህሉ ወደ ሥራ መመለሳቸውን ሚኒስቴሩ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው እና ወራሪው ህወሓት ጉዳት ከደረሰባቸው 42 ሆስፒታሎች ውስጥ 36 ያህሉ ወደ ሥራ መመለሳቸውን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር አየለ ተሾመ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ÷ በተደረገው የዳሰሳ ጥናት መረጃ መሰረት በአማራ ክልል 40 ሆስፒታሎች፣ 452 ጤና ጣቢያዎች፣ 1 ሺህ 728 ጤና ኬላዎች ፣ በአፋር ክልል 2 ሆስፒታል ፣ 24 ጤና ጣቢያዎች እና 52 ጤና ኬላዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በኦሮሚያ 6 ሆስፒታሎች፣ 21 ጤና ጣቢያዎች፣ 978 ጤና ኬላዎች ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝም 15 ጤና ጣቢያዎች፣ 348 ጤና ኬላዎች በግጭት ምክንያት አገልግሎት የተስተጓጎለባቸው ጤና ተቋማት መሆናቸው ተረጋግጧል ነው ያሉት፡፡

በአሸባሪው ቡድን ጉዳት ከደረሰባቸው 42 ሆስፒታሎች 36 ያህሉ ሙሉ ለሙሉ ወደ ሥራ መመለሳቸውን ሚኒስትር ዲኤታው ተናግረዋል።

ጉዳት ከደረሰባቸው ሆስፒታሎች ውስጥ 40 ያህሉ በአማራ ክልል ሁለቱ ደግሞ በአፋር ክልል እንደሚገኙ ነው የገለጹት።

ከዚህ ውስጥ 36 ያህሉ ጥገና ተደርጎላቸውና የህክምና መሣሪያዎቻቸው ተተክተው ሙሉ ለሙሉ ወደ ሥራ ገብተዋል ብለዋል፡፡

ስድስት ያህል ሆስፒታሎች ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች በመሆናቸው ወደ ነበሩበት ለመመለስ ያልተቻለ መሆኑንም አንስተዋል።

በተመሳሳይ በአማራ ክልል 414 ፣ በአፋር 20 ፣ በኦሮሚያ 33 የወደሙ ጤና ጣቢያዎችን ድንገተኛ እና መሰረታዊ የጤና አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በጦርነቱ ወቅት 124 አምቡላንሶች የተዘረፉ እና የወደሙ ሲሆን ÷ጉዳት የደረሰባቸውን የመጠገንና 13 አዳዲሲ አምቡላንሶችን የመላክ ሥራ እንደተከናወነ ነው ተብሏል።

ሚኒስቴሩ ከሐምሌ 2013 ዓ.ም ጀምሮ ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎችና ከዚያ ዉጭ ባሉ ጤና ተቋማት የጤና አገልግሎት ምላሽ ከ708 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት መድሃኒቶችና የህክምና ግብዓቶችን ለክልሎች ድጋፍ አድርጓል ብለዋል፡፡

ከፈደራል ሆስፒታሎች፣ በአዲስ አበበ ጤና ቢሮ ስር ከሚገኙ ሆስፒታሎች እና ከዩኒቪርሲቲ ሆስፒታሎች ግምታቸው ከ208 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ መድሃኒቶችና የህክምና ግብዓቶችን ለወደሙ ጤና ተቋማት ለመልሶ ስራ ማስጀመሪያ ድጋፍ ማድረግ መቻሉም ተገልጿል፡፡

በመላኩ ገድፍ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.