በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ሥጋት እንዲከበር የፌደራል ፀጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓሉ የሰላምና የደስታ ሆኖ እንዲያልፍ እና የዕምነቱ ተከታዮች ያለምንም የፀጥታ ሥጋት ያከብሩ ዘንድ የፌደራል ፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጸ፡፡
በአዲስ አበባና በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች የኅብረተሰቡን ሰላምና ደኅንነት ለማስከበር ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ስምሪት ገብቶ ተልዕኮውን በቁርጠኝነት እየተወጣ እንደሚገኝም ተጠቁሟል፡፡
ህብረተሰቡ በአካባቢው ለሰላም እንቅፋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮችን ሲመለከት የተለመደውን ጥቆማ በመስጠትና አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ ከፌደራል ፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ጎን በመሆን የድርሻውን እንዲወጣም ተጠይቋል፡፡
የፌደራል ፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ለክርስትና ዕምነት ተከታዮች፣ በግዳጅ ላይ ለሚገኙ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሠራዊት፣ የከተማና የክልል ፖሊስ አባላት እንዲሁም ሌሎች የፀጥታና ደህንነት ኃይሎችም የጋራ ግብረ-ሃይሉ የእንኳን አደረሳቸሁ መልእክት ማስተላለፉን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!