Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ፡፡
 
ፕሬዚዳንቷ ድጋፉን ያደረጉት በመዲናዋ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት ለሚኖሩ 300 ለሚሆኑ ወገኖች ነው፡፡
 
ፕሬዝዳንቷ በዚሁ ጊዜ በችግር ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን በመርዳት ረገድ ሁሉም ዜጋ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
 
በችግር ውስጥ የሚገኙና ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን በዘላቂነት ለማቋቋም የሚያስችሉ ስራዎች መከናወን እንዳለባቸውም ነው ያሳሰቡት፡፡
 
ከዚህ አኳያ በክፍለ ከተማው ዛሬ ከተደረገው ድጋፍ ባሻገር ሴቶችና ወጣቶችን በዘላቂነት የሚደግፍ ፕሮጀክት እየተተገበረ ስለመሆኑም ለአብነት ማንሳታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.