ስፓርት

ማንቼስተር ዩናይትድ ኤሪክ ቴን ሃግን በሦስት ዓመት ውል ማስፈረሙን አስታወቀ

By Alemayehu Geremew

April 21, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዙ እግር ኳስ ክለብ ማንቼስተር ዩናይትድ ኤሪክ ቴን ሃግን በሶስት አመት ውል ማስፈረሙን አስታወቀ።

የ52 አመቱን አሰልጣኝ ሊራዘም በሚችል የአንድ አመት ተጨማሪ ኮንትራት ለሶስት አመታት ከሆላንዱ አያክስ አምስተርዳም ማስፈረሙን ክለቡ ይፋ አድርጓል።

የእንግሊዙ ክለብ አሰልጣኙን ማስፈረሙን ተከትሎ ለአያክስ የኮንትራታቸውን ማካካሻ የሚከፍል ይሆናል።

አዲሱ አሰልጣኝ በውጤት ቀውስ የሚገኘውን ክለብ መልሶ የመገንባት ቀዳሚ ስራ ይጠብቃቸዋል ተብሏል።

የላንክሻየሩ ክለብ ከአሰልጣኝ አሌክስ ፈርጉሰን መልቀቅ በኋላ የሊግ ዋንጫ አሸንፎ አያውቅም።