Fana: At a Speed of Life!

አዲሱ የሩሲያ ሚሳኤል ጠላቶቻችን ደጋግመው እንዲያስቡ የሚያደርግ ነው -ፑቲን

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ሩሲያ በተሳካ ሁኔታ የሞከረችው አዲሱ ሚሳኤል ጠላቶቻችንን ደጋግመው እንዲያስቡ የሚያደርግ ነው” ሲሉ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተናገሩ፡፡

ሩሲያ ሳርማት የተባለውን አህጉር አቋራጭ ባላስቲክ ሚሳኤል የተሳካ ሙከራ ማድረጓን ሀገሪቱ የህዋ ምርምር ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

ከሚሳኤል ሙከራው በኋላ በሀገሪቱ ቴሌቪዥን ንግግር ያደረጉት ፕሬዚዳን ቭላድሚር ፑቲን የሩሲያን የህዋ ምርምር ኤጀንሲን እንኳን ደስ አላችሁ ያሉ ሲሆን “ይህ ፕሮጀክት የሞስኮ ጠላቶች ሁለት ጊዜ እንዲያስቡ የሚያደርግ ነው” ብለዋል፡፡

“ሚሳኤሉ የሩሲያን ወታደራዊ የውጊያ አቅም ያጠናክራል በተጨማሪም የሩሲያን ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ያረጋግጣል” ሲሉም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡

ሳርማት የተባለው አዲሱ አህጉር አቋራጭ ሚሳኤል በማንኛውም አህጉር ላይ የሚገኝን ኢላማ መምታት ይችላል ተብሏል፡፡

ሚሳኤሉ ከሰሜናዊ ምዕራብ ሩሲያ የተወነጨፈ ሲሆን ካምቻካ በተባለው የምስራቃዊ ሩሲያ ረግረጋማ ስፍራ ላይ ኢላማውን መምታት መቻሉን የሩሲያን ጦር ጠቅሶ አልጀዚራ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.