Fana: At a Speed of Life!

በተለያዩ ከተሞች ለግብይት ሊውሉ የነበሩ ከ84 ሺህ በላይ ሀሰተኛ የብር ኖቶች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቡሬ፣ ባሕር ዳር እና አዲስ አበባ ከተሞች ለግብይት ሊውሉ የነበሩ ከ84 ሺህ በላይ የብር ኖቶች መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ለእንስሳት ግብይትና የሆቴል አገልግሎት ተጠቅሞ ሊከፈል የነበረ በድምሩ ከሁለት ግለሰቦች ከ20 ሺህ ብር በላይ ሀሰተኛ የብር ኖት ከእነወንጀል ፈጻሚዎቹ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ ማድረግ መጀመሩን የቡሬ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር መልሰው አበበ ለአሚኮ ተናግረዋል።
በተመሳሳይ በባሕርዳር ከተማ በበላይ ዘለቀ ክፍለ ከተማ የበዓል ገበያን ተከትሎ በሀሰተኛ የብር ኖት ሊገበያዩ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በበላይ ዘለቀ ክፍለ ከተማ የከብት ግብይት በሚፈጸምበት ስፍራ በተደረገ ክትትል 60 ሺህ 200 ሀሠተኛ የብር ኖት የተያዘ ሲሆን፥ ግለሰቦቹ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የበዓል ሰሞን በሀሰተኛ የብር ኖቶች ለመገበያየት የሚደረጉ ሙከራዎች ሊበራከቱ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርም ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

በሌላ በኩል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሀሰተኛ  የብር ኖት በማዘዋወር የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች  በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

አንደኛው ተጠርጣሪ ወደ ባንክ በመሄድ ወደ አካውንቱ 3 ሺህ 500  ብር ገቢ ሲያደርግ÷ ከዚህ ውስጥ 1 ሺህ ሀሰተኛ ብር ቀላቅሎ አስገብቷል በሚል በባንኩ ሠራተኞች ጥርጣሬ ለፖሊስ በደረሰ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡

በተመሳሳይ የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቅ ባለቤት የሆነ ግለሰብ÷ ወደ ሱቁ እቃ ሊገዘ የመጣን ግለሰብ 3 ሺህ 400 ሀሰተኛ የብር ኖቶችን ከዚህ በፊት የሰጠኸኝ አንተ ነህ በማለት በተፈጠረ አለመግባባት ፖሊስ በቦታው ደርሶ ሲያጣራ ሆን ብሎ ግለሰቡን ለመወንጀል አስቦ ያደረገው መሆኑ በመረጋገጡ በቁጥጥር ስር መዋሉን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.