Fana: At a Speed of Life!

የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ ናይጄሪያ ለምዕራባውኑ ነዳጅ በመሸጥ በለስ ቀንቷታል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ኅብረት ዲፕሎማቶች ካሳለፍነው ሳምንት ወዲህ ከናይጄሪያ መንግስት የነዳጅ ኩባንያ ጋር 40 በመቶ የሚሆነውን የሀገሪቷን የነዳጅ አቅርቦት ለመግዛት መደራደራቸው ተሰምቷል፡፡

ምዕራባውያኑ ሩሲያ ላይ ማዕቀብ መጣላቸውን ተከትሎ ባጋጠማቸው የነዳጅ እጥረት እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የዋጋ ንረት ተከትሎ ነው ዓይኖቻቸውን በአፍሪካዊቷ ሀገር ላይ ያሳረፉት፡፡

የናይጄሪያ፣ የኒጀር እና የአልጄሪያ መሪዎችም ከሳምንታት በፊት በሰሃራ በኩል ወደ አውሮፓ የሚደርስ 4 ሺህ ኪሎ ሜትር የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ለመዘርጋት ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል፡፡

15 በመቶ የሚሆነውን የዓለም የኃይል አቅርቦት መሸፈን የሚያስችል የሃይድሮ ካርበን ክምችት ያላቸው የአፍሪካ ሀገራትም ከኃይል አቅርቦት ሽያጭ ለመጠቀም “ጊዜያችን አሁን ነው” በማለት ላይ ይገኛሉ፡፡

በተቃራኒው ናይጄሪያ የነዳጅ አቅርቦቷን በገፍ ወደ አውሮፓ መላክ መጀመሯን ተከትሎ ዜጎቿ በየዕለት መስተጋብራቸው ውስጥ በከፍተኛ የኃይል አቅርቦት ዕጦት እየተሰቃዩ እንደሚገኝ ዘ አፍሪካን ሪፖርት ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.