አዲስ ከተማ ክ/ከተማ 127 ቤቶችን ለተቸገሩ ወገኖች አስተላለፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 127 ቤቶች ለተቸገሩ ወገኖች ተላለፉ።
ቤቶች የተላለፈላቸው ነዋሪዎች ለረጅም ዓመታት በቤት ችግር ሲሰቃዩ ለነበሩና የድሀ ድሃ ተብለው ለተለዩ ነዋሪዎች መሆኑ ተመልክቷል።
ቤቶቹን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተገኝተው ማስረከባቸውን ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ለነዋሪዎቹ የተላለፉት ቤቶች በህገወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ መሆናቸውም ተገልጿል።