Fana: At a Speed of Life!

5 ሺህ ኪሎ ግራም በሚጠጋ ቅቤ ውስጥ ባዕድ ነገር ቀላቅለው ሊሸጡ በነበሩ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓላትን አስታከው 5 ሺህ ኪሎ ግራም በሚጠጋ ቅቤ ላይ ባዕድ ነገር ቀላቅለው ሊሸጡ በነበሩ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ፡፡
ሰሞኑን በሚዛን አማን ከተማ፣ በካፋ እና በቤንቺ ሸኮ ዞኖች በተካሄደ የዘመቻ ሥራ÷ 2 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር ግምት ያለው 4 ሺህ 849 ኪሎ ግራም ከባዕድ ነገር ጋር የተቀላቀለ ቅቤ ተይዟል፡፡
በዚህ ሕገ ወጥ ድርጊት በተሳተፉ 30 ነጋዴዎች ላይ አስተዳደራዊ እና ሕጋዊ እርምጃ መወሰዱን ከኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከባዕድ ነገር ጋር ተቀላቅሎ የተያዘው ቅቤ ለህብረተሰቡ ቢደርስ ከፍተኛ የጤና ችግር ያስከትል እንደነበርም ነው የተመላከተው፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.