Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያና ኮሪያ የሁለትዮሽ የልማት ትብብር ተጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁለትዮሽ የጋራ የልማት ትብብር ላይ ያተኮረ የኢትዮጵያና የኮሪያ ሪፐብሊክ የፖሊሲ የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ትብብር ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ሰመርታ ሰዋሰው ከ1940ዎቹ ጀምሮ በጠንካራ መሰረት ላይ የተገነባ መሆኑን ጠቁመው÷ ኮሪያ ለኢትዮጵያ የምትሰጠው የልማት ድጋፍ በትራንስፖርትና ኢነርጂ፣ በገጠር ልማት፣ በጤናና አካባቢ ንጽህና እንዲሁም በትምህርት ላይ ያተኮረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የኮሪያ ሪፐብሊክ የኢትዮጵያ ዘላቂ የልማት አጋር መሆኗን ጠቅሰው የኮሪያ ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ኤጀንሲ፣ የኮሪያ ኤግዚም ባንክና ሌሎች ሶስት የኮሪያ ዓለም አቀፍ የልማት ተቋማት በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የልማትና ኢንቨስትመንት ዘርፎች መሰማራታቸውን ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ የኮሪያ ሪፐብሊክ አምባሳደር ሚስተር ካንግ ሲኮሂ ኢትዮጵያ ለኮሪያ በጣም አስፈላጊ ወዳጅ መሆኗን ጠቁመው÷ ኮሪያ ለአፍሪካ ከምትሰጠው የልማት ድጋፍ የኢትዮጵያ ድርሻ 20 በመቶ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
የኮሪያ ዓለም አቀፍ የልማት ተቋማት በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚያከናውነው የልማት ተግባራት በተጨማሪ 20 የኮሪያ የግል ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተለያዩ የቢዝነስና የኢንቨስትመንት ዘርፎች ተሰማርተው ንቁ የልማት ተሳትፎ እያደረጉ መሆናቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.