Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል የመሠረታዊ አገልግሎቶችን ጥራት ለማሳደግ ከቱርክ የመጡ ከፍተኛ አማካሪዎች ጅግጅጋ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል የመሠረታዊ አገልግሎቶችን ጥራት ለማሳደግ ከቱርክ የመጡ ከፍተኛ አማካሪዎች እና የመንግስት ተወካዮች ጅግጅጋ ገብተዋል፡፡
በሶማሌ ክልል መሠረታዊ አገልግሎቶችን ለማሳደግ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ከቱርክ ሀገር የመጡት የመልቲ ኮንሰልቲንግ ድርጅትና የቱርክ መንግስት ተወካይ ፕሮፌሰር ዚያ ብሩሀቲን እና ሲይፍቲን ቦጋዚል ዛሬ ማምሻውን ጅግጅጋ ከተማ ገብተዋል።
ኃላፊዎቹ ጅግጅጋ ከተማ ገራድ ዊልዋል አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሶማሌ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሙሴ አህመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ከቱርክ የመጡ ከፍተኛ ኃላፊዎችና አማካሪዎች ከዚህ ቀደም በተደረገ የሁለትዮሽ ውይይት መሰረት ወደ ክልሉ መምጣታቸው ተመላክቷል፡፡
ኃላፊዎቹ በክልሉ ቆይታቸው የጤና ሽፋንና ጥራትን ለማሳደግ፣ በክልሉ የሚገኙ ሆስፒታሎች አገልግሎትን ለማሻሻል እገዛ ለማድረግና እንደ ሙከራ ፕሮጀክት በተመረጡ አካባቢዎች ሆስፒታሎች በሚገነቡበት ሁኔታ ላይ ምክክር እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
በከተሞች እድገት፣ በእርሻና መስኖ ልማት ፣ ፋይናንስንና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን በመደገፍ ከክልሉ ጋር ተባብሮ ለመስራት የሚያስችል ውይይቶች ይካሄዳሉ ሲል የክልሉ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.