Fana: At a Speed of Life!

በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት ታስቦ ዋለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በዛሬው ዕለት ታስቦ ውሏል፡፡
ዕለቱ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በስግደት፣ በጸሎት እና በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች ነው የታሰበው፡፡
በተለይም ስቅለት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በስግደትና በጾም የታሰበ ሲሆን÷ በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረትም በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች ታስቦ ውሏል፡፡
በአብያተ ክርስቲያናቱ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጅን ለማዳን ሲል የተቀባላቸውን መከራዎች ለማስታወስ የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶች ቀርበዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.