Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ለኢትዮጵያ 313 ሚሊየን ዶላር የሚጠጋ ተጨማሪ የሰብዓዊ ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በነበረው ግጭት ጉዳት ለደሰረባቸው ዜጎች የሚውል 313 ሚሊየን ዶላር የሚጠጋ ተጨማሪ የሰብዓዊ ድጋፍ ማድረጓን አስታውቃለች፡፡
 
ድጋፉ በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤይድ) በኩል በአማራ፣ አፋር እና ትግራይ ክልሎች በግጭቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የሚሰራጭ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
 
የተደረገው ድጋፍ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ለመድረስ፣ የጤና ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎት ለማሻሻል ፣ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል ፣ የጾታ ጥቃቶችን እና የሥነ ልቦና ችግሮችን ለመቀነስ ይውላልም ተብሏል፡፡
 
አሜሪካ በቀጣይ የችግር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ለመርዳት ቁርጠኛ መሆኗ የተገለጸ ሲሆን ÷ ለዚህም የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች በአማራ፣ አፋር እና ትግራይ ክልሎች ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የሚያደርጉትን የሰብዓዊ ድጋፍ አጠናክረው መቀጠላቸው ተጠቁሟል፡፡
 
ዩናይትድ ስቴትስ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ግጭት ከተቀሰቀሰ ጀምሮ እስካሁን 995 ሚሊየን ዶላር የሚወጣ የሰብዓዊ ድጋፍ ማድረጓንም ዩ ኤስ ኤይድ ጉዳዩን አስመልከቶ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል ፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.