Fana: At a Speed of Life!

አስተዳደሩ ለተቸገሩ ወገኖች 2 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የበዓል ስጦታ አበረከተ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ችግር ላይ ለሚገኙ ዜጎች ከ2 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የበዓል ስጦታ አበርክቷል፡፡
 
የአስተዳደሩ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ካሳሁን እምቢያለ እንደተናገሩት÷ በከፍተኛ ችግር ላይ ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ዜጎች፣ ለዘማችና ለዘማች ቤተሰቦች የተደረገውን ድጋፍ ጨምሮ ከ2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የተለያዩ የበዓል ስጦታዎች ተበርክተዋል፡፡
 
በዛሬው ዕለት ለ91 ዘማችና የዘማች ቤተሰቦች ከ378 ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸው የበዓል ስጦታዎች እንደተበረከቱ ገልጸዋል፡፡፡
 
በዓሉ የመደጋገፍና የአብሮነት በመሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች በዓሉን ሲያከብሩ ካላቸው በማካፈል እና የሌላቸውን በማገዝ መሆን እንዳለበትም ተቀዳሚ ከንቲባው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
 
በታለ ማሞ
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.