Fana: At a Speed of Life!

ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ምቹ ሁኔታ እንፈጥራለን- አቶ ንጉሱ ጥላሁን

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ምቹ ሁኔታ እንፈጥራለን ሲሉ የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ገለጹ፡፡
አቶ ንጉሱ በጀሞ ሸማቶች እና ኢንተርፕራይዞች የሚገናኙበት ባዛር ላይ እየተሳተፋ ከሚገኙ ኢንተርፕራይዞች ጋር ተወያይተዋል። ሚኒስትር ዴኤታው በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት÷ ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አቅማቸውን የሚያሳድጉበት ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር በቅንጅት ይሰራል።
የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራዝ አንቀሳቃሾች በበኩላቸው፥ ባዛሩ ደንበኛ ያፈሩበት እና የገበያ ትስስር የፈጠሩበት መሆኑን አንስተው፥ ሰፊ ጊዜና ቦታ እንዲሁም ተከታታይነት ያለው ባዛር እንዲዘጋጅ ጠይቀዋል።
አቶ ንጉሱ በባዛሩ የታዩ እና በኢንተርፕራይዞች የተነሱ መልካም ልምዶችን ለማስፋት እና የተነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ እንሰራለን ብለዋል።
እስከ ነገ ድረስ የሚቆየው ይህ ባዛር በቀጣይ ለሚዘጋጁ ተመሳሳይ መርሐ ግብሮች ልምድ የተቀሰመበት መሆኑም ተመላክቷል፡፡
በቅድስት አባተ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.