Fana: At a Speed of Life!

የኬንያ የቀድሞው ፕሬዚዳንት መዋይ ኪባኪ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኬንያ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሙዋይ ኪባኪ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

የኬንያ ሶስተኛው ፕሬዚዳንት እና አገሪቱን ከፈረንጆቹ 2003 እስከ 2013 የመሩት ኪባኪ በተወለዱ በ90 ዓመታቸው በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፥ የኪባኪን ህልፈት ተከትሎ በመላ አገሪቱ ብሄራዊ የሀዘን ቀን መታወጁን አስታውቀዋል፡፡

ለክብራቸው ሲባልም የአገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ በሎ እንዲውለበለብ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል፡፡

ኪባኪ ኬንያን በአስቸጋሪ ወቅት ከመምራታቸው ባለፈ የአገሪቱ ኢኮኖሚ ወደ ላቀ ደረጃ እንዲደርስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸው ይነገራል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.