Fana: At a Speed of Life!

1ሺህ 149 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳዑዲ ዓረቢያ የመመለስ ስራ 1ሺህ 149 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተገለፀ፡፡

ከተመላሾቹ መካከል 14ቱ ሕፃናት ሲሆኑ፥ 1 ሺህ 135ቱ ወንዶች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ለተመላሾቹ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጁላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ መደረጉን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ቁጥራቸው ከ12 ሺህ 800 በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.