Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ለ837 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ837 ህግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን የክልሉ ፍትህ ቢሮ አስታወቀ፡፡

የክልሉ ፍትህ ቢሮ ሃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ ÷ የይቅርታ ሂደቱ በወንጀል ሕጉ ላይ የተቀመጠውን የይቅርታ አዋጅ መርህ ተከትሎ የተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል ፡፡

ታራሚዎቹ ከተወሰነባቸው የእስራት ጊዜያት መካከል አንድ ሦስተኛውን ማጠናቀቃቸውን በተለያዩ ደረጃ በሚገኙ የህግ አካላትና በክልሉ ይቅርታ ቦርድ ተጣርቶ የቀረበ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በማረሚያ ተቋማት በሚቆዩበት ወቅትም በየጊዜው በተለያዩ የሕግ አካላት የሚሰጠውን የማነጽ ተግባራት በተገቢው ተቀብለው የባህሪ ለውጥ ማሳየታቸው የተመስከረላቸው ናቸው ብለዋል፡፡

በይቅርታ አዋጅ ውስጥ የማይካተቱ የወንጀል ፍርደኞች መኖራቸውን ያስረዱት የቢሮው ሃላፊ ለአብነትም ከፌዴራል ማረሚያ ተቋም በአደራ እንዲቆዩ የተደረጉ በክልሉ የይቅርታ ቦርድ የማይታዩ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ይቅርታ ተጠቃሚ የሆኑ ታራሚዎች በቆይታቸው የተሰጣቸውን የማነፅ ትምህርት በተገቢው በተግባር ላይ በማዋል ሕብረተሰቡን መካስ እንደሚጠበቅባቸው ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.