Fana: At a Speed of Life!

በአቶ አህመድ ሽዴ የተመራው ልዑክ ከብሪታንያ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ የተመራው ልዑክ ከብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ቪኪ ፎርድ ጋር በሁለትዮሽና በኢኮኖሚ ትብብር ጉዳዮች ላይ ተወያየ።

አቶ አህመድ ሽዴና ቪኪ ፎርድ የተወያዩት በሁለትዮሽ እና የኢኮኖሚ ትብብር ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መሆኑ ተገልጿል።

በውይይቱ የኢትዮጵያና ብሪታንያን የኢኮኖሚ ትብብር ለማጠናከር በሚያስችል ጠቀሚ ጉዳዮች ላይ መምከራችውንም ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር የሆኑት ቪኪ ፎርድ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፥ ከገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ጋር ያደረጉት ውይይት በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው የሰላም ሂደት፥ በአሁኑ ወቅት አስፈላጊ ስለሆነው የሰብዓዊ አቅርቦት እና ብሪታንያ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ኢትዮጵያውያን ዜጎች ሁሉ ማድረግ ስላለበት ድርጋፍ ተወያይተናል ብለዋል።

ውይይታቸውም ስኬታማ እንደነበር አመላክተዋል።

በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሺዴ የተመራው ልዑክ በዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ዋሺንግተን ዲሲ መግባቱ የሚታወስ ሲሆን÷ በቆይታው ከስብሰባው ባለፈ የሁለትዮሽና የባለ ብዙ ወገን ምክክር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ እና የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ ከገንዘብ ሚኒስትሩ ጋር ወደስፍራው ማቅናታቸው ተገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.