በጋምቤላ ክልል የትንሳኤ በዓል በሰላም እንዲከበር ዝግጅት መደረጉን ፖሊስ ገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የትንሳኤ በዓልን ያለ ምንም የፀጥታ ስጋት እንዲከበር አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አቡላ ኡቦንግ አስታወቁ።
ኮሚሽነሩ እንደገለጹት ÷በዓሉ በሰላም እንዲከበር አስፈላጊው የጸጥታ ኃይል ስምሪት ተደርጓል።
በተለይም በጋምቤላ ከተማና አካባቢው የስርቆትና የዘረፋ ወንጀሎች በሚፈጸምባቸው የስጋት ቀጠናዎች የክልልና የፌዴራል ፖሊስ ጥምር ኃይል መሰማራታቸውን ተናግረዋል።
ኮሚሽኑ በተለይም በጋምቤላ ከተማና አካባቢው በሕዝባዊ ውይይት መድረኮች እንደ ችግር የተነሱበትን የስርቆትና የዘረፋ ወንጀሎች ለመቀነስ የ90 ቀናት እቅድ አውጥቶ እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።
በዚህም እየተከናወኑት ባሉ ወንጀልን የመከላከል ስራዎች በጋምቤላ ከተማና አካባቢው በስርቆትና በዘረፋ ወንጀል የተጠረጠሩ በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ ነው ብለዋል።
ኅብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ ወንጀልን ለመከላከል እየተደረገ ያለው ሁሉን አቅፍ ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮሚሽነር አቡላ አስታውቀዋል።
የክልሉ ነዋሪዎችም ለፀጥታ ስጋት የሚሆኑ ጉዳዮች ሲያጋጥሟቸው ፈጥነው ለፖሊስ እንዲጠቁሙ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!