Fana: At a Speed of Life!

በሀረሪ ክልል የሸዋል ኢድ በዓል አከባበር በተሳካ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ሚያዚያ 14፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀረሪ ክልል የሸዋል ኢድ በዓል አከባበር በህዝቦች እና በሃይማኖቶች መካከል ፍቅርን፣ መቻቻልንና አብሮነትን ሊያጠናክር በሚችል መልኩ ለማክበር እየተሰራ መሆኑን የ የክልሉ ርዕሰ መስተደድር አቶ ኦርዲን በድሪ ተናገሩ፡፡

የሀረሪ ክልል ካቢኔ በክልሉ በተለይም ከሸዋል ኢድ በዓል ጋር በተያያዘ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን ገምግሟል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት፥ በክልሉ ከሸዋል ኢድ በዓል ጋር ተያይዞ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት ማጠናከርና የበዓሉ አከባበር የተሳካ ማስቻል ያስፈልጋል ብለዋል።

በክልሉ በልዩ ሁኔታ የሚከበረው የሸዋል ኢድ በዓል ሲከበርም በዋናነት በብሔር ብሔረሰቦች እና በሃይማኖቶች መካከል አብሮነትን፣ መቻቻልንና መደጋገፍን ሊያጠናክር በሚችል መልኩ እንዲከበር ለማስቻል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በተለይም ከከተማ ፅዳትና ውበት አንፃር የሀረርን ታሪክ የሚመጥኑ ስራዎች ከማከናወንና በዓሉ ካለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ከማስቻል አንፃር ህዝብን ባሳተፈ መልኩ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል።

ከዚህ ባሻገርም በእንግዳ ተቀባዩ የክልሉ ህዝብ ለበዓሉ የሚመጡ እንግዶች ተገቢውን አቀባበል እንዲያደርግ ከማድረግና እንግዶቹም አስደሳች ቆይታ እንዲኖራቸው ለማስቻልም እየተሰሩ የሚገኙ ተግባራትን ማጠናከር ይገባል ማለታቸውን ከሀረሪ ከሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.