Fana: At a Speed of Life!

የገንዘብ ሚኒስትሩ ከዓለም ባንክ የቀጠናው ተወካይ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ከዓለም ባንክ የምሥራቅና የደቡባዊ አፍሪካ አገራት ተወካይ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ስለሚሰጠው ድጋፍና በሌሎች በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

በዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ዓመታዊ ስብሰባ ጉን ለጎን የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ከቀጠናው የዓለም ባንክ ተወካይ ጋር ባካሄዱት ውይይት፥ የኢትዮጵያ መንግስት የአየር ንብረት ለውጥ እና እየጨመረ ያለውን የዋጋ ንረት እና ሌሎች ተግዳሮቶችን ለማቃቀለል እያደረገ ያለውን ጥረት ለዳሬክተሩ አስረድተዋቸዋል፡፡

ሚኒስትሩ እና የዓለም ባንክ ተወካይ በሪፎርም ሂደት፣ በባንኩ ፖርትፎሊዮ አፈጻጸም እና በዓለም ባንክ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይም መክረዋል።

ሚኒስትሩ የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ በተከሰተው ግጭት የተጎዱ ወገኖችን ለማቋቋም ለነደፈው ፕሮጀክትና ከዚህ ቀደም ላደረገው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በዚሁ ወቅት የዓለም ባንክ የቀጠናው ዳይሬክተር ሚስተር ኦስማን ዲዮን በበኩላቸው÷ በሂደት ላይ ያሉትን ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ለማድርግ ያላቸውን ቁርጠኝነት ማረጋገጠቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.