Fana: At a Speed of Life!

10 ክላሽና 2 ሺህ የሚጠጉ ጥይቶችን በአገዳ በመደበቅ ሲያጓጉዝ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በታሰረ አገዳ ውስጥ 10 ክላሽና ከ1 ሺህ 900 በላይ ጥይቶችን ደብቆ ሲያጓጉዝ የነበረ ግለሰብ ከነተሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ዋለ።

በደቡብ ወሎ ዞን የለጋምቦ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ተወካይ ምክትል ኢንስፔክተር መሐመድ አደም እንደገለጹት፥ ሚያዚያ 10 ቀን 2014 ዓ.ም በተደረገ ክትትልና ፍተሻ ህገ ወጥ የጦር መሣሪያዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋል ተችሏል ብለዋል።

መነሻውን ደሴ አድርጎ ወደ ወግዲ በመሄድ ላይ የነበረ ኤፍ ኤስ አር የጭነት መኪና አገዳ፣ ዘይትና ሌሎች ሸቀጦች ጋር አብሮ በማሰር 10 ክላሽ፣ 1 ሽህ 9 መቶ 38 የክላሽና 105 የብሬን ጥይት ሲያጓጉዝ አቀስታ ከተማ ላይ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታውቋል።

ህገ ወጥ የጦር መሣሪያ መልሶ ኅብረተሰቡን የሚያጠፋ መሆኑን በመረዳት ማኀበረሰቡ ለጸጥታ ኃይሉ አጋዥ ሆኖ ህገ ወጦችን እንዲያጋልጥም ፖሊስ ጥሪ ማቅረቡን ከወረዳው ኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.