ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአማራ ክልል ዋግኽምራ ዞን የሰቆጣ ከተማ ማዕከላዊ እዝ እና ማኅበረሰቡን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፋሲካ ዋዜማ በአማራ ክልል ዋግኽምራ ዞን የሰቆጣ ከተማ ማዕከላዊ እዝ እና ማኅበረሰቡን ጎብኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከማኅበረሰቡ አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት፣ የአገው ሕዝብን የኪነ-ህንፃ ልህቀት እና ፍልስፍናዊ መሰረት አድንቀዋል።
እነዚህን እሴቶች የመጠቀም እና ፈተናዎችን ለማሸነፍ አንድነትን ማስጠበቅ ያለውን ጠቀሜታ አመልክተዋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአካባቢው የሚስተዋለውን የግጭት ሁኔታ አንስተው፣ ሰላምን ማስፈን የሰላማዊ ወኪል ለመሆን ወስኖ በቁርጠኝነት የሰላም እሴቶችን መገንባትን ይጠይቃል ማለታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ÷ ከጉብኝቱ ጎን ለጎን ከዋግኽምራ ዞን ማኅበረሰብ ጋር እንደተወያዩ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በውይይቱ ላይ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል ተመሥገን ጥሩነህ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ምክትል ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልል የሥራ ኀላፊዎች መገኘታቸውን ታውቋል።