Fana: At a Speed of Life!

ጂቡቲ ወደብ የደረሰውን 50 ሺህ ሜትሪክ ቶን ዩሪያ የአፈር ማዳበሪያ ማጓጓዝ ተጀምሯል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ስታር ፒክሰስ” የተባለችው መርከብ የመጀመሪያውን 50ሺህ ሜትሪክ ቶን ዩሪያ ማዳበሪያን ይዛ ትናንት ምሽት ጅቡቲ ወደብ ገብታለች፡፡

እስካሁን “ኤን.ፒ.ኤስ.ቢ” እና “ኤን.ፒ.ኤስ” የተሰኙ የአፈር ማዳበሪያ ዓይነቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንደገቡ ታውቋል፡፡

ዛሬ ደግሞ ዩሪያ ወደ ሀገር ውስጥ የማጓጓዝ ሥራ መጀመሩን ከባህርና ትራንስፖርት ሎጀስቲክስ ድርጅትያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የ”ስታር ፒክሰስን” ጨምሮ እስካሁን በ10 መርከቦች ከ540 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ማዳበሪያ ወደብ የደረሰ ሲሆን፣ በመጪው ሳምንት መጨረሻ በሦስት መርከቦች ተጨማሪ 180 ሺህ ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ወደብ ይደርሳልም ተብሏል፡፡

ወደብ ከደረሰው ማዳበሪያ ከ 455 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ የሚሆነው ወደ ሀገር መዳረሻ ጣቢያዎች መጓጓዙም ተመልክቷል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.