Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ መንግስት በኬንያው የቀድሞ ፕሬዚዳንት መዋይ ኪባኪ ሕልፈት የተሰማውን ሃዘን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግስት በኬንያው የቀድሞ ፕሬዚዳንት መዋይ ኪባኪ ሕልፈት የተሰማውን ሃዘን ገልጿል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ÷ መዋይ ኪባኪ በሕይወት በነበሩበት ጊዜ የነበራቸው ራዕይ ሩቅ እንደነበረና በአመራራቸውም ለኢትዮጵያና ኬንያ ኢኮኖሚያዊ ትሥሥር እና የሁለትዮሽ ትብብር እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መንገድ እንደጠረጉ አውስቷል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት ይህን አሳዛኝ ወቅት ከወዳጅ የኬንያ መንግስት እና ህዝብ ጋር እንደሚጋራም በመግለጫው ተመላክቷል፡፡

መንግስት ኪባኪ በሕይወት ዘመናቸው ኢትዮጵያንና ኬንያን የበለጠ ለማቀራረብ የሠሩትን የማኅበራዊ አገልግሎት ሥራ አንስቶም አድንቋል፡፡

መንግስት ለኬንያ ህዝብ ፣ ለሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች እንዲሁም የሥራ ባልደረቦች ልባዊ መፅናናትን ተመኝቷል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.