Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ለ456 ወጣቶችና ሴቶች 91 ሼዶችን አስረከቡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድርግ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ለ456 ወጣቶችና ሴቶች የስራ እድል የሚፈጥር 91 ሼዶችን ለተጠቃሚዎች አስረከቡ፡፡
 
ከንቲባዋ በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ ለወጣቶች እና ሴቶች ባስተላለፉት መልእክት ሼድ ማግኘት በራሱ ግብ ሳይሆን በረትቶ መስራትንም ይጠይቃል ብለዋል፡፡
 
ብዙዎች ችግራችን የተለያየ ቋንቋ መናገር ከተለያየ ብሄር መገኘታችን አድርገው ያቀርባሉ፤ ነገር ግን ዋናው ችግር ድህነት መሆኑን የገለጹት ከንቲባዋ ÷ መለወጥ ያለብን በኢኮኖሚ ነው ብለዋል፡፡
 
ለዚህም ሰርተን ተግተን ሌትና ቀን ፤ህይወታችንን በሚለውጥ አካባቢን በሚለውጥ ተግባር ላይ ጉልበታችንንም ጊዜያችንንም እውቀታችንንም ማዋል ይኖርብናል ፤ ተባብሮ መስራትና ስንፍናን ማስወገድ ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡
 
ሴቶች እና ወጣቶች በህይወታችሁ ላይ አዲስ ትንሳኤ ማምጣት አለብን፤ በትልቅ ተነሳሽነት ልትሰሩ ይገባል ሲሉመ አሳስበዋል፡፡
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ መላኬ አለማሁ በበኩላቸው÷ አስተዳደሩ የስራ እድል ፈጠራ ስራ ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
 
ዋና ስራ አስፈፃሚዋ እስካሁን 182 ሼዶችን በበጀት ዓመቱ ማስረከብ እንደተቻለ መግለጻቸውን ከከንቲባ ጽህፈትቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ ሲሉመ አሳስበዋል
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.