Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ አዲሱን የሳርማት ሚሳኤል የታጠቀ ወታደራዊ ክፍል ልታሰማራ ማቀዷን ገለፀች

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ አዲሱን የሳርማት ሚሳኤል የታጠቀ ወታደራዊ ክፍል በዚህ ክረምት ልታሰማራ ማቀዷን አስታውቃለች፡፡

ወታደራዊ ክፍሉ ከሞስኮ በስተምስራቅ 3000 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው በክራስኖያርስክ ግዛት ውስጥ በምትገኘው ኡዙር ስፍራላይ እንደሚሰማራ የሩሲያ የጠፈር ኤጀንሲ ሃላፊ ዲሚትሪ ሮጎዚንን ጠቅሶ ታስ የዜና ምንጭ ዘግቧል፡፡

ሩሲያ ሳርማት የተባለውን አህጉር አቋራጭ ባላስቲክ ሚሳኤል የተሳካ ሙከራ ማድረጓን አገሪቱ የህዋ ምርምር ኤጀንሲ ከቀናት በፊት ማስታወቁ የሚታወስ ነው፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.