የአማራ ክልል ለ3 ሺህ 141 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል የትንሳኤ በዓልን እና የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ ለ3 ሺህ 141 ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ገረመው ገብረፃድቅ በሰጡት መግለጫ በክልሉ ካሉ ታራሚዎች ውስጥ 3 ሺህ 85 ወንድ እና 56 ሴት ታራሚዎች በድምሩ ለ3 ሺህ 141 ታራሚዎች ምህረት ተደርጎላቸዋል።
ታራሚዎቹ የሚጠበቅባቸውን የእርማት መጠን ያጠናቀቁ እና ምህረት በማያሰጡ የአስገድዶ መድፈር፣ መሰረተልማትን የማውደምና ሙስና ወንጀል ያልተሳተፉ እና የተለያዩ ወንጀሎች ፈፅመው ካጠናቀቁት የእስራት መጠን ባለፈ እርቅ እና ካሳ መፈፀማቸው የተረጋገጠላቸው መሆኑን ተናግረዋል።
ምህረት የሚሰጣቸው ከወረዳ ጀምሮ ባሉ የይቅርታ እና የእርቅ መፈፀምን የሚከታተል እና ሌሎችም አሰራሮች መኖራቸውን ገልጸዋል።
ይህ ምህረት እስከሚሰጥበት የመጨረሻው የክልሉ የይቅርታ ቦርድ ተገቢነቱ የሚጣራበት መሆኑን ሃላፊው አብራርተዋል።
በፀጋዬ ወንድወሰን