Fana: At a Speed of Life!

የትንሳኤ በዓልን ስናከብር አንድነታችንን በማጠናከር እና ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሠላም በመስራት ሊሆን ይገባል-የሃይማኖት አባቶች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓልን ስናከብር አንድነታችንን በማጠናከር እና የኢትዮጵያን ዘላቂ ሠላም ለማስፈን በተግባር በመስራት ሊሆን ይገባል ሲሉ የሃይማኖት አባቶች አሳሰቡ፡፡
 
በክርስትና ዕምንት ተከታዮች ዘንድ በነገው ዕለት የሚከበረውን የትንሳኤ በዓል በማስመልከት የሃይማኖት አባቶቹ የእንኳን አደረሳችሁ መከልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
 
“የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ የሰው ልጅ ሃጥያት የተሰረየበት ፣ ፍቅር የተገኘበት እንዲሁም እንዲሁም ደህንነት የተጎናፀፈበት ነው” ብለዋል፡፡
 
በዓሉን በተለያየ ምክንያት ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን በመደገፍ እና በመንከባከብ ማሳለፍ እንደሚገባም የሃይማኖት አባቶቹ አሳስበዋል፡፡
 
በኢትዮጵያ እየተስተዋሉ የሚገኙ የሠላም መደፍረሶች ዋጋ እያስከፈሉ ነው፤ ይህም አስቸኳይ መፍትሄ ሊያገኝ ይገባልም ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
 
ህዝበ ክርስቲያኑም በመላ ሀገሪቱ ሠላም እንዲሰፍን ጥረቱን እንዲያጠናክር የሃይማኖት አባቶቹ ጠይቀዋል፡፡
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.