Fana: At a Speed of Life!

በአቶ አህመድ ሽዴ የተመራው ልዑክ ከቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን መስራች እና ሊቀመንበር ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአቶ አህመድ ሽዴ የተመራው የልዑካን ቡድን ከቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን መስራች እና ተባባሪ ሊቀመንበር ከሆኑት ሜሊንዳ ጌትስ ጋር ተወያየ፡፡
በውይይታቸው ፋውንዴሽኑ በኢትዮጵያ በጤና፣ግብርና እና ዲጂታል ዘርፎች እያከናወናቸው ስላሉ ተግባራት መክረዋል፡፡
በዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ዓመታዊ ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ ያለው ልዑክ ከስብሰባው ጉን ለጎን ከዓለም ባንክ የምሥራቅና የደቡባዊ አፍሪካ አገራት ተወካይ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን፣ከብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ቪኪ ፎርድ ጋር እንዲሁም ከሌሎች አለም አቀፍ አካላት ጋር በሁለትዮሽና በኢኮኖሚ ትብብር ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ እና የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ ከገንዘብ ሚኒስትሩ ጋር ወደስፍራው ማቅናታቸው ይታወሳል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.