የሀገር ውስጥ ዜና

አንጋፋው የማስታወቂያ ባለሙያው አቶ ውብሸት ወርቃለማው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

By Tibebu Kebede

March 01, 2020

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 22፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አንጋፋው የማስታወቂያ ባለሙያው አቶ ውብሸት ወርቃለማው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

አቶ ወብሸት ባደረባቸው ህመም በቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው ትናንት ነበር ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት።

በኢትዮጵያ የማስታወቂያ ኢንዱስትሪ ውስጥ ፈር ቀዳጅ የነበሩት አቶ ውብሸት፥ አንበሳ የተባለ የማስታወቂያ ድርጅት በመክፈት በዘርፉ ሲሰሩ ቆይተዋል።

በተጨማሪም አቶ ውብሸት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን አባል በመሆን ሀገራቸውን በመወከል የህዝብ ለህዝብ ግኑኝነትን በማሻሻሉ የድርሻቸውን ተወጥተዋል።