ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የትንሳዔ በዓልን ከአቅመ ደካሞች ጋር አከበሩ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካሞች የምሳ ግብዣ አደረጉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከ230 በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች ነው በዓሉን ምክንያት በማድረግ ግብዣ ያደረጉት፡፡
አቅመ ደካሞቹ ጧሪ የሌላቸው አረጋውያን፣ ህይወታቸውን በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚመሩ አካል ጉዳተኞች፣ ከጎዳና ላይ የተነሱ ልጆች እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ “በዓሉን ሁላችንም አቅም የሌላችውን በመርዳት፡ ያለው ለሌለው በማካፈል መንፈስ ልናከብረው ይገባል” ብለዋል።
በአልአዛር ታደለ