አቶ አህመድ ሽዴ ከአይ ኤም ኤፍ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም /አይ ኤም ኤፍ/ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጊቫ ጋር ተወያዩ ፡፡
በውይይታቸው የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ማጠናከር በሚቻልበት እንዲሁም በግጭት እና በድርቅ ሳቢያ የተከሰቱት ችግሮች ለመፍታት በሚቻልበት ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋሙ ውይይቱ ውጤታማ እንደነበርም በፌስ ቡክ ገፁ አስፍሯል፡፡
በዋሺንግተን ዲሲ እየተካሄደ በሚገኘው በዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ዓመታዊ ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ ያለውና በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የተመራው ልኡክ ከስብሰባው ጎን ለጎን ከተለያዩ አለም አቀፍ አካላት ጋር እየተወያየ ይገኛል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!