Fana: At a Speed of Life!

የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለተፈናቀሉ ዜጎች እና ለጸጥታ አካላት ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ወሎ ዞን የትንሳኤ በዓልን በማስመልከት በ1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ለተፈናቀሉ ዜጎች እና ለጸጥታ አካላት ማዕድ አጋርቷል፡፡
የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አብዲ ሰይድ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት÷ ለመከላከያ ሰራዊት ፣ለአማራ ልዩ ሀይል እና ከትግራይ ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች እንዲሁም ከኦሮሚያ ክልል ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው ለመጡ ዜጎች የማዕድ ማጋራት ስነ ስርዓት ተካሂዷል፡፡
አቶ አብዲ እንደተናገሩት ÷ወቅቱ መረዳዳትን የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉም የአቅሙን ሊያደርግ ይገባል ፡፡
ማዕድ ማጋራቱ በሀይቅ ከተማ ጃሪ መጠለያ የተካሄደ ሲሆን ÷በስራ ላይ ለሚገኙ የጸጥታ አካላትም ባሉበት እንዲደርስ ተደርጓል፡፡
ፈናቃዮቹ በዓልን በተለየ መልኩ እንዲያሳልፉ ላደረጉ አካላት ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ÷ የሚደረጉ ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
በከድር መሀመድ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.