Fana: At a Speed of Life!

ከ10 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በተለያዩ ከተሞች ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ ከተሞች ለሚገኙ ድጋፍ ለሚሹ እና አነስተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖች ከ10 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ ተደርጓል፡፡

በዚሁ መሰረት በአዳማ ከተማ ከ7 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ከ2 ሺህ 900 በላይ ወገኖች የበዓል መዋያ ድጋፍ መደረጉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በደቡብ ወሎ ዞን በተሁለደሬ ወረዳ ጊዜያዊ መጠለያ ለሚገኙ ወገኖች ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ የተደረገ ሲሆን÷ በተመሳሳይ በሰቆጣ ከተማ እና አካባቢው ተጠልለው ለሚገኙ ወገኖች የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የአይነት ድጋፍ መደረጉን አሚኮ ዘግቧል፡፡

በተመሳሳይ በጎንደር ከተማ ከ600 በላይ ለሚሆኑ ወገኖች፣ በቲሊሊ ከተማ ከ120 በላይ ድጋፍ ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ በፍኖተ ሰላም ከተማ ከ100 ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጪ ማዕድ የማጋራት መርሀሐ ግብሮች ተከናውነዋል፡፡

በተመሳሳይ በባሕር ዳር ከተማ ከ1 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወገኖች እና በፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለሚገኙ ሕሙማን እና አስታማሚዎች እንዲሁም ለሆስፒታሉ ሠራተኞች ከ150 ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጪ ማዕድ የማጋራት መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡

በአርባምንጭ ከተማ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከ200 በላይ ለሚሆኑ ወገኖች ማዕድ የማጋራት መርሐ ግብር እና የአይነት ድጋፍ መደረጉን ከጋሞ ዞን ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.