Fana: At a Speed of Life!

የአድዋ ድል በአልን ምክንያት በማድረግ በደብረ ብርሃን የ8 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 22፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) 124ኛውን የአድዋ ድል በአልን ምክንያት በማድረግ በደብረ ብርሃን ከተማ የ8 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ።

በአትሌት ፋንቱ ሚጌሶ በተዘጋጀው የጎዳና ላይ ሩጫ ላይ ከተለያዩ ክለቦች የመጡ አትሌቶችና የከተማዋ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

ውድድሩን የኢትዮጵያ ስፓርት አካዳሚ ዴይሬክተር አቶ አንበሳው እንየውና የኢትዮጵያ አንጋፋ አትሌቶች ማህበር ዋና ፀሀፊ አትሌት ይበልጣል ያልፈው ውድድሩን አስጀምረውታል።

በሩጫው በሴቶች በላይነሽ ውበቴ ከደብረ ብርሃን አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል በበላይነት ስታጠናቅቅ ከበቡሽ ይስማው በግል፣ ትዕግሥት ገዛኽኝ ከፌዴራል ፖሊስ 2ኛ እና 3ኛ በመሆን አጠናቀዋል።

በወንዶች ቢኒያም አወቀና ዳዊት ሀብቴ ከደብረብርሃን አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል 1ኛ እና 2ኛ ሲወጡ መንገሻ ጸጋዬ በግል 3ኛ በመሆን ውድድሩን ጨርሰዋል።

ለአሸናፋ አትሌቶችም የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቷል ።

በአበበ የሸዋልዑል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.