Fana: At a Speed of Life!

በኮንሶ ዞን ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች ከ8 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የአይነት ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ በኮንሶ ዞን ለሚገኙ በግጭት ምክንያት ለተፈናቀሉ እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ወገኖች 8 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የአይነት ድጋፍ ተደረገ፡፡
የተደረገው ድጋፍ የምግብ ዘይት፣ ስኳር እና አልባሳትን ያካተተ ሲሆን÷ በሰገን ዙሪያ እና ካራት ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃይ እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ወገኖችተበርክቷል፡፡
የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እንደገለጹት ÷ ምንም እንኳን የተለያዩ ችግሮች ቢኖሩብንም ያለንን ማካፈል፣ የታረዘውን ማልበስ፣ የተራበን ማጉረስ እና ለተቸገሩ መድረስ አብሮን ያደገ ባሕል ነው።
በሰገን ዙሪያ ወረዳ እና በኮልሜ ክላስተር በተከሰተው የጸጥታ ችግር ምክንያት ከ35 ሺህ በላይ ተፈናቃይ ወገኖች መኖራቸውን ጠቅሰው÷ ከ8 ሚሊየን 263 ሺህ 700 ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ አድርገናል ማለታቸውን ከኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.