Fana: At a Speed of Life!

አርቲስት ዘነቡ ገሠሠ ከዚህ አለም በሞት ተለየች

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አርቲስት ዘነቡ ገሠሠ ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች፡፡

አርቲስቷ ባደረባት የጡት ካንሰር ህመም በሕክምና ስትረዳ ቆይታ ነው በዛሬው ዕለት ሕይወቷ ማለፉ የተሰማው፡፡

አርቲስት ዘነቡ ገሠሠ በርካታ የጥበብ ሥራዎች ላይ በመሳተፍ እና ድንቅ ብቃቷን በማሳየት አድናቆትን አትርፋለች፡፡

አርቲስት ዘነቡ የሁለት ሴቶች እና የሁለት ወንድ ልጆች እናት ነበረች ፡፡

የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ነገ ሚያዝያ 17 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 9:00 ሰዓት በቡልቡላ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን እንደሚፈፀም ለማወቅ ተችሏል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትም በአርቲስቷ ሞት የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ÷ ለወዳጅ ዘመዶቿ እና ለአድናቂዎቿ መፅናናትን ይመኛል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.