Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ በሶማሌ ክልል ድርቅ ለተከሰተባቸው አከባቢዎች ማቋቋሚያ 338 ሚሊየን ብር መደበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ድርቅ ለተከሰተባቸው አከባቢዎች ማቋቋሚያ 338 ሚሊየን ብር መመደቡን የመስኖና ቆላማ አከባቢ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ የሚተገብራቸውን የማቋቋሚያ ሥራዎች ማሳወቂያ መርሃ ግብር በጅግጅጋ ከተማ አካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ በቆላማ አከባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት በኩል በሶማሌ ክልል ድርቅ በተከሰተባቸው አከባቢዎች የማቋቋሚያ ሥራዎቹ እንደሚከናወኑ ተገልጿል።

ከዓለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በ338 ሚሊየን ብር ይከናወናልም ነው የተባለው።

በማሳወቂያ መርሃ ግብሩ ላይ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ፣ የመስኖና ቆላማ አከባቢ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ እና ሌሎች የፌደራልና የሶማሌ ክልል የሥራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.