Fana: At a Speed of Life!

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ተፈናቅለው ለሚገኙ ዜጎች አፋጣኝ እርዳታ እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአምስት ወራት ያህል በሽብር ቡድኑ ህወሃት ቁጥጥር ስር በቆየው የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ውስጥ ተፈናቅለው ለሚገኙ ዜጎች አፋጣኝ እርዳታ እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ፡፡
ዓለም አቀፍ ረጂ ተቋማትም በሚፈለገው ልክ እርዳታ እንዳያቀርቡም ሀሰተኛ የሆነ የደህንነት ስጋትን በምክንያት እያቀረቡ መሆናቸው ለችግሩ መባባስ ምክንያት እንደሆነም ነው የተገለፀው፡፡
የተራድኦ ተቋማቱ ዋነኛው የደህንነት ስጋት ያለበት ብለው የሚገልጹት ይህንኑ ወረዳ ቢሆንም ፣ ስጋታቸው ከእውነታው ጋር የማይጣጣም እንደሆነም ተጠቁሟል።
በብሄረሰብ አስተዳደር ዞኑ በየጊዜው የሚጨምረውን የተፈናቃዮች ቁጥር የሚመጥን ድጋፍ ያለመገኘቱ ፈተናውን አግዝፎታል ነው የተባለው።
በስፍራው የሚገኙ ተፈናቃዮችም የጦርነቱ ተጽዕኖ ኑሯቸውን በማናጋቱ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉም አካላት አፋጣኝ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሹመት ጥላሁን ÷ የጦርነቱ ተጽዕኖ አስቀድሞም በቋሚ የሴፍትኔት ፕሮግራም እርዳታ ሲያገኝ የቆየውን ማህበረሰብ ኑሮ ይበልጡኑ ያናጋው በመሆኑ ለሰብዓዊነት የላቀ ቦታ በመስጠት ያለ ምንም ስጋት ድጋፍ ማድረስ እንደሚቻል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በዞኑ ጥብቅ የሆነ ፀጥታን የማስጠበቅ ስራ እየተሰራ መሆኑን ነው አስተዳዳሪው የጠቆሙት፡፡
በበርናባስ ተስፋዬ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.