በመኖሪያ ቤት ውስጥ የተነሳ የእሳት ቃጠሎ በሰው ህይወት ላይ ጉዳት አደረሰ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ወሎ ዞን ኩታበር ወረዳ 05 ቀበሌ ትናንት ምሽት 2 ሰዓት አካባቢ ከመኖሪያ ቤት ውስጥ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ የ80 ዓመት አዛውንት እናት ህይወት አለፈ፡፡
አዛውንቷን ለማዳን ሙከራ ስታደርግ የነበረችው ልጅም መጠነኛ ጉዳት ደርሶባት በህክምና መረዳቷ ተገልጿል።
ቃጠሎው በቤት ውስጥ ከተከመረ የከብት ሳር የተከሰተ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ÷ ከጥንቃቄ ጉደለት የተከሰተው አደጋ ወደ ጎረቤት እና ሌሎች ቦታዎች እንዳይዛመት የከተማውና የአካባቢው ነዋሪዎች ከጸጥታ ሃይሉ ጋር ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል ነው የተባለው።
ነዋሪው ከመሰል የእሳት አደጋዎች ለመጠበቅ ጥንቃቄ በማድረግ በተለይም ህፃናትን እና በእድሜ የገፉ ሰዎችን አደጋ ሊከሰትልባቸው ከሚችሉ ቦታዎች እንዲጠበቁ ማድረግ እንደሚገባ መልዕክት መተላለፉን ከኩታበር ወረዳ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!