Fana: At a Speed of Life!

በመጪው ዓርብ ታላቅ የጎዳና ላይ የኢፍጣር መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ይካሄዳል – ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጪው ዓርብ ታላቅ የጎዳና ላይ የኢፍጣር መርሐ ግብር በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የ”ከዒድ እስከ ዒድ” አስተባባሪ ኮሚቴ አስታወቀ።
መርሐ ግብሩን ለመታደም እንግዶች ከተለያዩ የዓለም አገራት ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ላይ እንደሚገኙ ነው የኮሚቴው ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ ያሳወቁት።
ከዒድ እስከ ዒድ ጥሪን ለማስተባበር እስካሁን ከ2 ሺህ 500 በላይ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ተሳትፈዋል ያሉት ኡስታዝ አቡበከር፣ በመጪው ረቡዕ የዒድ ኤክስፖ መርሐ-ግብር እንደሚከፈትም መግከለጻቸውን ኢፕድ ዘገባ ያመላክታል።
የኢፍጣር መርሐ ግብሩ የኢትዮጵያን በጎ ጎን ለዓለም ማስተዋወቂያ ዕድል እንደሚፈጥርም ኡስታዝ አቡበከር ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ቀደም ሲል “ታላቁ የዒድ ሰላት በኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል “ከዒድ እስከ ዒድ ወደ አገር ቤት” እንዲገቡ ለኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ለኢትዮጵያ ወዳጆች በጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.