በኦሮሚያ በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎች እንዲያገግሙ በትኩረት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎች እንዲያገግሙ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የመስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ በኦሮሚያ ክልል በቆላማ አካባቢ ለድርቅ የተጋለጠው የማህበረሰብ ክፍል ከድርቁ እንዲያገግም በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ገልጾ ለዚሁ ዓላማ የሚውል 6 ሚሊየን 395 ሺህ 993 ብር ለክልሉ መንግስት አስረክቧል፡፡
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት÷ በቆላማ አካባቢ የሚኖረው ማህበረሰብ እንዲያገግም የተጀመረው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በበኩላቸው÷ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው መንግሥት በድርቅ የተጎዱ ወገኖችን በዘላቂነት ለማቋቋም እንደሚሠራ ገልጸዋል፡፡
በኢዶሳ አብዲ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!