Fana: At a Speed of Life!

በአቶ አህመድ ሺዴ የተመራ ልዑክ ከአሜሪካ የተለያዩ ተቋማት የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ የተመራ ልዑክ ከአሜሪካ የተለያዩ ተቋማት የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያየ።
 
ልዑኩ ከአሜሪካ የግምጃ ቤት፣ የውጭ ጉዳይ፣ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት፣ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ውጤታማ ውይይት አድርጓል።
 
በውይይቱ ወቅት በሃገራቱ ታሪካዊ፣ ስትራቴጂክ እና በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
 
ውይይቱ በዋናነት በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማቶች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነበር ተብሏል።
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.