Fana: At a Speed of Life!

የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ 74 ተሽከርካሪዎች ዛሬ መቐለ ደረሱ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ 74 ተሽከርካሪዎች በዛሬው ዕለት መቐለ መድረሳቸውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታውቋል፡፡

አሁን ላይ የሰብዓዊ እርዳታው መቐለ በሚገኝ መጋዝን ውስጥ እየተራገፈ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

ከ200 ሺህ ሜትሪክ ቶን የሰብዓዊ እርዳታው በተጨማሪም 5 ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች መኖራቸው ተመላክቷል፡፡

የሰብዓዊ እርዳታውን በክልሉ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች ለማሰራጨት ዝግጅት መደረጉን የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ባሳለፍነው ቅዳሜ በሶስተኛው ዙር 74 እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ከአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በአባአላ መንገድ በኩል ወደ መቐለ ማምራታቸው መግለጹ ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.