Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ተጨማሪ የጦር መሳሪያ ለዩክሬን መላኳን እንድታቆም ሩሲያ አስጠነቀቀች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ለዩክሬን ተጨማሪ የጦር መሳሪያ መላኳን እንድታቆም ሩሲያ አስጠነቀቀች።
በዋሺንግተን የሩሲያ አምባሳደር አናቶሊ አንቶኖቭ ቀደም ሲል አሜሪካ በርከት ያሉ የጦር መሳሪያዎችን ለዩክሬን ስትልክ ይህ ድርጊት አግባብ እንዳልሆነ እና ተቀባይነት እንደሌለው ገልጸን ነበር ብለዋል።
አያይዘውም አሜሪካ ከዚህ ሀላፊነት የጎደለው ተግባር ልትታቀብ ይገባል ማለታቸውን ከሮሲያ 24 ቴሌቪዝን ጣቢያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል።
ከአሜሪካ የሚመጡ እንዲህ ያሉ የጦር መሣሪያ ድጋፎች ሁኔታውን ይበልጥ እንደሚያባብሱት ሊታወቅ ይገባልም ብለዋል አምባሳደሩ፡፡
በሚያዝያ ወር መጀመሪያ ላይ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለዩክሬን ወታደራዊ እርዳታ የሚውል ተጨማሪ 800 ሚሊየን ዶላር እርዳታ እንደምትሰጥ መግለጻቸውን አስታውሶ ኢልና ኒውስ ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.